አንቺ ደፋር በሉኝ ዛሬ በአማርኛ ነው የምፅፊው።ዛሬ ክላስ ሆኜ አንድ ቀን እንግልዝኛ አወራሽ ብሎ ሊቆጣኝ የቃጣው ሰውየ ትዝ አለኝ። ኮስተር ኮራ ብሎ ነበር “I am a teacher.” ያለኝ። አሁን አሁን ወጣቱን ለመተቸትና ጥፋተኛ ለማረግ፣አንድ አንዱም የአለማወቁን ቁጭትና ንዴት አክሎ እንግልዝኛ ተናጋሪውን ከልቡ ጠልቶታል ይሳለቅበታል። 

ደፈር ሲልም ቆጣ ይላል።

ይህም ሰውየ በመምህርነቱ፣ በእውቀቱ ኮርቶ ነበር እንግልዝኛዬን በእንግልዝኛ ሲመክር የነበረው። እናም ቅድም ራሴን ስጠይቅ ይህ ክፍል የምንማረው Organic chemistry, Thermodynamics ምናምን የኛ ነው እንዴ? Integration, Derivation ምናምን ባላውቅ አቶ መምህር ጉድ ሊል ነው።

የኛ የኢትዮጵያውያን ትምህርት መልእክተ ዮሀንስ እና መዝሙረ ዳዊት ነበር ከዛም የጓዳው ዶሮና ጠጁ። ቋንቋ እንኳ ባሁን ግዜ ይህ ተብሎ አይያዝም። እርግጥ የራስን የመሰለ የለም ነገር ግን የራስህንስ ከየት አመጣኸው መባሉም አለ። እነ አክሱም እንኳ ከግብፅና ከአረብ ቀላቅለው ያመጡትን የራሴ ትላለህ?አስኳላ ብልህ አማርኛ school ብልህ እንግልዝኛ ልትለኝ ነው?

ያንን የቋንቋ አርበኛ መምህር ኢትዮጵያዊ ባልሆነው የምህንድስና እና የህክምና እውቀቱ ልቆጣው ይሆን?

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s